البحث

عبارات مقترحة:

الأكرم

اسمُ (الأكرم) على وزن (أفعل)، مِن الكَرَم، وهو اسمٌ من أسماء الله...

التواب

التوبةُ هي الرجوع عن الذَّنب، و(التَّوَّاب) اسمٌ من أسماء الله...

المجيد

كلمة (المجيد) في اللغة صيغة مبالغة من المجد، ومعناه لغةً: كرم...

ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት በጣሀ አህመድ

الأمهرية - አማርኛ

المؤلف
القسم مقالات
النوع نصي
اللغة الأمهرية - አማርኛ
المفردات ليلة القدر - العشر الأواخر
ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት በጣሀ አህመድ  ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት በጣሀ አህመድ الأيام الأخيرة من رمضانየእነዚህን አሰርት የረመዳን ቀናት በተለይም ለሊቶችን ታላቅ ደረጃ የሚሰጣቸው ስለመሆኑ የተለያዩ ነጥቦችን ማንሳት ቢቻልም ዋና ዋናዎቹን ለመጠቆም እወዳለሁ፡-የረመዳን ወር ታላቅ ወር መሆኑ ለሁላችንም ግልጽ ነው፡፡ ስለታላቅነቱም ብዙ ሳንሰማ ወይም ሳናነብ አልቀረን ይሆናል፡፡ የረመዳን ወር የላቀ ታላቅ ወር እንደመሆኑ ሁሉ ከቀናቶቹና ከለሊቶቹ የመጨረሻዎቹ አስሩ ለየት ያለ ቦታ ሊሰጣቸው የሚገቡ ናቸው፡፡ እነዚህን አሰርት የረመዳን ቀናት በተለይም ለሊቶች ታላቅ ደረጃ ልንሰጠቸው እንደሚገባ የሚያመለክቱ የተወሰኑ ነጥቦችን በአጭሩ ለመጥቀስ እወዳለሁ፡፡አንደኛ፡- የአላህ መልዕክተኛ በነዚህ አስርት ቀናት እና ለሊቶች የነበራቸው የአምልኮ ሁኔታ የምዕመናን እናት ዓኢሻ (ረዲየላዑ ዓንሀ) እንዲህ ብለዋል፡፡ ‹‹የአላህ መልዕክተኛ ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ከሌላ ጊዜ በተለየ መልኩ (በዒባዳ) ላይ ይተጉ ነበር›› ሙስሊም ዘግበውታል የአላህ መልዕክተኛው የለሊቱ አብዛኛውን ክፍል ከእንቅልፍ በመራቅ ህያው ያደርጉት ነበር፡፡ አሁንም ዓኢሻ (ረዲየላዑ ዓንሀ)  እንዲህ ብለዋል፡፡ ‹‹ የአላህ መልዕክተኛ ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አሰርት ቀናት ሲገባ ለሊቱን በዒባዳ ላይ በማሳለፍ ህያው ያደርጉ፣ ቤተሰባቸውን ያነቃቁ (ይቀሰቅሱ) ፣ ቀበቷቸውን በማጥበቅ ይተጉ ነበር፡፡›› ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል          በሐዲሱ ውሰጥ ‹‹ቀበቷቸውን ያጠብቁ ነበር›› በሚል የተጠቀሰውን ቃል በተመለከተ ብዙ የሐዲስ ተንታኞች እንዳሉት ‘‘አሽሙራዊ አገላለፅ ሲሆን ለማለት የተፈለገውም በከፍተኛ ሁኔታ በዒባዳ ከመጠመዳቸው በመነሳት ከሴቶቻቸው ይርቁ ነበር ለማለት ነው’’ ፡፡ሁለተኛ፡- የእነዚህን አሰርት ቀናት እና ለሊቶች ታላቅነት የሚያሳየን በውስጣቸው ‹‹ለይለተል ቀድር›› የተባለችው ለሊት መኖር ነው፡፡ ይህች ለሊት ከሌሎች የምትለይበት ብዙ መለያዎች ያላት ስትሆን ከነርሱም መካከል፡-1.     ቁርአን የወረደባት ለሊት መሆኗ2.     ከአንደ ሺህ ወራት የምትበልጥ መሆኗ3.     የተባረከች መሆኗ4.     ጅብሪል  በመልዕክት በብዛት የሚወርዱባት መሆኗ5.     ሰዎች በከፍተኛ አምልኮ ውሰጥ የሚገቡ ከመሆኑ አንፃር ከእሳት ሰላም ወይም ነፃ የሚወጡባት ለሊት መሆኗ6.     በዚህች ለሊት አላህ ምንዳውን እንደሚከፍለው በእርግጠኝነት በማመን እንዲሁም ከይዩልኝ እና መሰል ዱንያዊ ፍላጐቶች ርቆ ሰላትን መስገድ ያበዛ ወንጀሉ የሚታበስ መሆኑ ነው፡፡ሶስተኛው፡-  በእነዚህ አስር ቀናት ኢዕቲካፍ መግባት የመልዕክተኛው ሱና ነው፡፡ ኢዕቲካፍ ማለት እራስን ለአምልኮ ብቻ በመወሰን በመስጂድ መዘውተር ነው፡፡ እናታችን ዓኢሻ እንዲህ ብለዋል፡፡ ‹‹ነብዩ እስኪሞቱ ድረስ ከረመዳን የመጨረሻዎቹን አስርት ቀናት እራሳቸውን ለአምልኮ ብቻ በመወሰን በመስጂድ ይዘወትሩ ነበር፡፡›› ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውተልE ከዚህ በመቀጠል ከኢዕቲካፍ ጋር ተያያዥነት ያለውን ይህንን ፈትዋ ወይም ጥያቄና መልስ እንመለከታለን፡፡ጥያቄ፡- የኢዕቲካፍ መስፈርቶች የትኞቹ ናቸው? ፆም ከመስፈርቶቹ ይካተታልን? አንድ ሰው በኢዕቲካፍ ላይ እያለ በሽተኛን መጠየቅ፣ በግብዣ ቦታ ላይ መገኘት፣ የቤተሰቦቹን ጉዳይ ማስፈፀም፣ አስክሬን መሸኘት ወይም ወደ ስራው መሄድ ይችላልን?መልስ፡- ሰላተል ጀመዓ በሚሰገድባቸው መስጂዶች ውስጥ ኢዕቲካፍ ማድረግ የተደነገገ ነው፡፡ ነገር ግን ኢዕቲካፍ የሚያደርገው ግለሰብ ሰላተል ጁምዓ ግዴታ ከሚሆንባቸው ሰዎች መካከል ከሆነና ከኢዕቲካፍ ቀናት መካከል የጁምዓ ቀን ካለ ሰላተልጁምዓ በሚሰገድበት መስጅድ ውስጥ ኢዕቲካፍን ማድረጉ የተሻለ (በላጭ) ነው፡፡ ፆም የኢዕቲካፍ መስፈርት አይደለም፡፡ እንዲሁም በኢዕቲካፍ ላይ ያለ ሰው በዚያ ወቅት በሽተኛን አለመጠየቁ፣ ጥሪ ቢቀርብለት በጥሪ ቦታ ላይ አለመገኘቱ፣ የቤተሰቦቹን ጉዳዬች አለማስፈፀሙ፣ አስክሬን አለመሸኘቱ፣ ከመስጂድ ውጪ ወደ ስራው አለመሄዱ ሱና ነው፡፡ ይህም እናታች ዓኢሻ በትክክለኛ ሰነድ እንዲህ ማለታቸው የተረጋገጠ በሆኑ ነው፡፡ ‹‹በኢዕቲካፍ ላይ ያለ ሰው በሽተኛን አለመጠየቁ፣ የአስክሬን አሸኛኘት ላይ አለመገኘቱ፣ ግንኙነትን አለመፈፀሙም፣ በስሜት ከተቃራኒ ፆታ ጋር አለመተሻሸቱ፣ አስገዳጅ ለሆነ ጉዳይ ቢሆን እንጂ ከኢዕቲካፍ አለመውጣቱ ሱና ነው፡፡›› አቡዳውድ እና ዳረቁጥኒ ዘግበውታልቋሚ የፈትዋ ኮሚቴአብዱላህ ቢን ቁዑድአብዱረዛቅ ዓፊፊአብዱል ዓዚዝ ኢብን ባዝ

التفاصيل

المرفقات

2

ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት በጣሀ አህመድ
ከረመዳን የመጨረሻዎቹ አስርት ቀናት በጣሀ አህመድ